ቴስቴስትሮን ወንድን ወንድ የሚያሰኘው ሆርሞን ሲሆን ከጥቅሞቹም መካከል ለጡንቻና አጥንት እድገት ፤ ለጉርምስና ምልክቶች መውጣት ለምሳሌ በብብትና በብልት አካባቢ ፂም መውጣት ፤ ለብልት ማደግ ፤ እንዲሁም ለወሲብ ፍላጎት መኖር በጣም አስፈላጊ ሆርሞን ነው።
ዝቅተኛ የደም ውስጥ የቴስቴስትሮን መጠን የተለያዩ ችግሮችን በወንዶች ላይ ያስከትላል ከነዚህ መካከል
– ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት(Low Libido)
– የአቅም ማጣት (low energy)
– ትኩረት ማጣት(Lack of concentration)
– የጡንቻዎች ማነስ (Low Muscle mass)
– ለአጥንት መሳሳት (osteoporosis)
– በተጨማሪም ለልብና ለ ደም ግፊት ተጋላጭነትን ይጨምራል።
የደም ውስጥ ቴስቴስትሮን መጠን በጉርምስና ወቅት በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ዕድሜ እየገፋ ሲመጣ ማለትም ከ40 ዓመት በኋላ የመቀነስ ባህሪ ያሳያል። በዚህም ምክንያት ነው በጎልማሶች ላይ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች የሚስተዋሉት።
በተፈጥሮአዊ መንገድ የቴስቴስትሮንን መጠን መጨመርያ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው።
1) ክብደትን መቀነስ
ወፍራም ሰው በተፈጥሮ ከፍተኛ የሆነ የስብ ክምችት አለው ። ስብ ደግሞ በደም ውስጥ የሚገኘውን testestron ወደማይፈለግ Estradiol (የሴቶች ሆርሞ ) ወደተባለ ሆርሞን የሚቀይር ኢንዛይም ስላለው የቴስቴስትሮንን መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል።
ስለዚህ ክብደት መቀነስ በጥናት የተረጋገጠ ቴስቴስትሮንን መጠን በከፍተኛ መጠን የመጨመሪያ መንገድ ነው።
2) የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ( Exercise )
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ መጠን ያለው ያካል ብቃት እንቅስቃሴ ለምሳሌ እንደ ክብደት ማንሳት ያለ እንቅስቃሴ (high intensity exercise ) የቴስቴስትሮን መጠን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል።
3) በቴስቴስትሮን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
ዝቅተኛ ስብ ያላቸው ምግቦችን መመገብ (ጮማን ማስወገድ)
ቱና፤ ቀይ የከብት ስጋ( Beef ) ፤የሼል አሳ (Shell fish) ፤ የእንቁላል ቢጫው ክፍል ፤ ነጭ ሽንኩርት የመሳሰሉት ምግቦች የቴስቴስትሮንን መጠንን ይጨምራሉ።
4) ጥሩ እንቅልፍ (Good Sleep)
በአሜሪካ በ2300 ወጣቶች ላይ በተሰራ ጥናት መሰረት የእንቅልፍ ሰዓትን በ1 ሰዓት መቀነስ የቴስቴስትሮን ን መጠን በስድስት ከመቶ (6%) ይቀንሳል ።ሌሎችም ጥናቶች በተደጋጋሚ እንዳሳዩት ጤናማ እና መደበኛ እንቅልፍ ለቴስቴስትሮን መጨመር ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ አለው።
5) ከተለያዩ ኬሚካል ካላባቸው ነገሮች መራቅ
ለምሳሌ Bisphenol-A የተባለው ኬሚካል በኮስሞቲክሶችና በፕላስቲክ በታሸጉ ምግብና መጠጦች ዉስጥ ሊገኝ ይችላል። እነዚህ ኬሚካሎች ቴስቴስትሮን እንዳይመረት እንደሚያደረጉ ተረጋግጧል። ስለሆነም BPA Free የሚሉ ምርቶችን ብቻ መጠቀም አስፈላጊ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ቴስቴስትሮን በሃኪም ትዕዛዝ በሚቀባ ወይም በ ኢንጄክሽን መልኩ ሊታዘዝ ይችላል።
ልብ ይበሉ የቴስቴስሮን ምርመራና ህክምና በኤፔክስ ሴክሽዋል ክሊኒክ ይገኛል።