አንድ ወንድ ቶሎ የመጨረስ ችግር አለበት የሚባለው ግኑኝነት ከጀመረ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሲጨረስ ወይንም እርሱ ወይንም አጋሩ ከምትፈልገው ጊዜ በታች ያለምንም ቁጥጥር የዘር ፈሳሽ ሲያፈስ ነው።
ይህም ችግር ከ30 እስከ 40 በመቶ በሚሆኑ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ይህም ቁጥር የችግሩን መጠኑ ሰፊነት ያሳያል።
ለመሆኑ ይህ ችግር መፍትሔ አለውን?
በአጭሩ መልሱ አዎ መፍትሔ አለው ነው። የህክምና አማራጮቹንም በ 3 ክፍሎ ማየት ይቻላል።
1) Behavioural therapy/ የባህሪ ህክምና
ይህ የህክምና አይነት የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የግንኝነት ቆይታን ማራዘም ነው :: ለምሳሌ
A) መጀመር ከዛ ማቆም (start and stop method ) ግኑኝነነት እያደረጉ ልክ ሊጨርሱ ሲደርሱ ለ30 second ያህል ብልቱን ከሴቷ ብልት በማውጣት ማቆየት ከዛ በኋላ መልሶ መጀመር :: ከ 3 እስከ 4 ጊዜ መደጋገም ፣ ይህንን ማድረግ ወንዱ የተሻለ ቁጥጥር እንዲኖረው ያደርጋል።
2) መያዝ (squeeze method)
ይህ ማለት ወንዱ ሊረጭ ሲል ብልቱን በማውጣት የብልቱን ጫፍ በመጠኑ ለ30 ሰከንድ ያክልመያዝ። ይህንንም ከ 3 እስከ
4 ጊዜ መደጋገም ።
3) በግኑኝነት ጊዜ ሌላ ነገር ለማሰብ መሞከር (distructed thinking)
4) ኪግል የመቀመጫ ስፖርት (Kegel exercise )
B) ማማከር (Counciling)
የችግሩ ምክንያት ከ ሳይኮሎጂካል ችግር ፤ ፤ከተዛባ ግንኙነት ( relationship issues ) ወይንም ከአስተሰሰብ ችግሮች ለምሳሌ ከጭንቀት ፤ ድብርት ፣ ከጥፋተኝነት ስሜት (guilt) ፣ የራስ መተማመን አለመኖር (Lack of self confidence ) የሚመጣ ከሆነ በpsycho therapy ይታከማል ።
C) የመድሀኒት ህክምና
የተለያዩ በሀኪም የሚታዘዙ መድሀኒቶች ሲኖሩ እነዚህም
A) Selective serotonin reuptake inhibitors የሚባሉ የሚዋጡ መድሃኒቶች
B) በብልት ላይ የሚነፉ እና በብልት አካባቢ የሚገኙትን ነርቮቹ በማደንዘዝ ከመጠን በላይ የብልት ቆዳዎች ሲነኩ ስሜታዊ እንዳይሆኑ የሚያደረጉ መድሃኒትች ( numbing cream and sprays)
C) ቶሎ የመርጨት ችግር ከስንፈተ ወሲብ ጋር አብሮ የመጣ ከሆነ እንደ ቪያግራ እና ሲያሊስ ያሉ መድኃኒቶችም ሊታዘዙ ይችላል።