የስንፈተ-ወሲብ (Erectile dysfunction) እና የቶሎ መጨረስ (premature ejaculation) ችግሮች ልዩነት እና ህክምናው?

Erectile dysfunction (የብልት አለመቆም) ችግር የምንለው የወንድ ልጅ ብልት አለመቆም ወይንም ከቆመ በሗላ እንደቆመ አለመቆየት (failure to attain or maintain erection) ማለት ሲሆን   ቶሎ መጨረስ( Premature ejaculation) ተከሰተ የምንለው ደሞ አንድ ወንድ ልጅ ከሚፈልገው የጊዜ ቆይታ በፊት ከ ቁጥጥሩ ውጪ ቀድሞ ሲረጭ ነው :: ቀድሞ የምንለው ቡዙ ጊዜ ከአንድ ደቂቃ በፊት ሲሆን ነው።

ከ 30 እስከ 40 ፐርሰንት የሚሆኑት ወንዶች ቀድሞ የመጨረስ ችግር እንዳለባቸው ጥናቶች ያሳያሉ። ይህ ችግር በ ወንድ ልጅ ወይም በ ፆታዊ አጋሩ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።

አንድ ወንድ ቀድሞ የመጨረስ ችግር አለበት የሚባለው ግንኙነት በተጀመረ ከአንድ ደቂቃ በፊት ሲረጭ ወይንም የሚረጭበትን ጊዜ መቆጣጠር ሲያቅተው ነው፡ ፡

ቶሎ የመጨረስ ችግር መንስኤ በአብዛኛው ጊዜ የ ሳይኮሎጂካል ወይንም  የስነ ልቦናዊ ችግር ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አካላዊ( Physical) ችግር ሊሆን ይችላል።በወሲብ ጊዜ ያለ ጭንቀት ወይም በራስ መተማመን አለመኖር ወይንም የጥፋተኝነት ስሜት ለቶሎ መጨረስ ችግር ሊዳርጉ ይችላሉ።

ቶሎ የመጨረስ ችግር የሚታከም ችግር ነው። ህክምናውም የተለያዩ ናቸው ዋነኛው ህክምና የባህሪ ህክምና( behavioural therapy)ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የመድሀኒት ህክምና ነው። ብዙ ጊዜ ይህ ችግር በሁለቱም የህክምና አማራጮች መታከም ይኖርበታል።

  ልብ ይበሉ Viagra( sildenafil citrate)ለቶሎ መጨረስ ችግር መፍትሔ አይደለም። Viagra  ለ ስንፈተወሲብ ወይንም erectile dysfunction የሚታዘዝ መድሀኒት ነው ::ዓላማውም ብልት ቀጥ ብሎ እንዲቆም ወይም እንዳይተኛ የሚያደርግ ነው።

ስንፈተ ወሲብ (Erectile  Dysfunction) የሚባለው ችግር ደግሞ የብልት መቆም አለመቻል ወይንም ቆሞ አለመቆየት ችግር ሲኖር ነው።

  ስንፈተ ወሲብ (Erectile  dysfunction) በአብዛኛው ዕድሜያቸው ገፋ ባለ ወንዶች ማለትም ከ 40 እስከ 70 ዓመት ባሉት ላይ የሚከሰት ሲሆን ሃምሳ ፐርሰንት(50%) የሚሆኑት በዚህ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወንዶችን ያጠቃል።

አንድ ወንድ ስንፈተ ወሲብ አለበት የሚባለው የብልት አለመቆም ሲኖር ወይንም ብልት ለመቆም ረጅም ደቂቃ መነካካት ሲኖርበት አልያም ቆሞ  አለመቆየት ወይም መልፈስፈስ ሲኖር ነው።

ስንፈተ ወሲብ ተጓዳኝ የጤና ችግር መኖሩን አመላካች ሊሆን ስለሚችል ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።ለምሳሌ ከስኳር በሽታ ፤ ከሆርሞን ችግር ፤ ከልብ በሽታ  እንዲሁም ከነርቭ በሽታ ጋር ሊያያዝ ስለሚችል ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው