ለወሲብ ብቃት የሚረዱ ምግቦች እና አጋዥ ንጥረ ነገሮች: ሳይንሳዊ

የግንኙነት ፍላጎት ለመጨመር የሚሆኑ ምግቦች ሳይንሳዊ መነሻ አላቸው ወይ ? እነማን ናቸው?

ወንድ እና ሴት ግንኙነት ለማድረግ ያላቸው ፍላጎት በሆርሞን ቁጥጥር ስር ነው። ለወንዶች testosterone ለሴቶች ደግሞ estrogen እና progesterone የሚባሉ ሆርሞኖች ተፅዕኖ ያሳድራሉ። ስለዚህ እነዚህን ሆርሞኖች የሚጨምሩ ምግቦች አሉ።

ሌሎቹ ምግቦች ደግሞ አንጐላችን ላይ የሚሰሩ ናቸው እነዚህም አንጐላችን ላይ ያለዉን serotonin የተባለዉን የሚጨምሩ ናቸው። ሴሬቶኒን የሚባለው ሲጨምር ዘና ( Relax) እንድንል የሚረዳ ነው። ሌላኞቹ ምግቦች ደግሞ የደም ፍስትን ወደ ሴትም ሆነ ወደ ወንድ ብልት የሚሄደውን ደም ፍሰት የሚጨምሩ ሲሆኑ እነዚህ የወሲብ መነቃቃት ስሜትን ይጨምራል።

የግንኙነት ፍላጎት ለመጨመር የሚሆኑ ምግቦች፦

1. UብUብ

በተለይ ለወንዶች UብUብ ሲመገቡ ለግንኙነት ያላቸው መነሳሳት ይጨምራል። ምክንያቱ ደግሞ በውስጡ L-citrulline የተባለ የፕሮቲን መስሪያ ኬሚካል በብዛት ይይዟል። ይሄ ደግሞ ናይትሪክ ኦክሳይድ የተባለውን ጋዝ እንዲመነጭ እና የደም ስሮች ተለጥጠው ወደ ብልት የሚሄደውን የደም ፍሰት ይጨምራል

2. L- arginine የተባለውን ያላቸው ምግቦች

ለምሳሌ ብዙ ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ( እንቁላል ፣ ዶሮ፧ አሳ ፣ ቀይስ)፣ ባቄላ ፣ ኦተር ምስር የመሳሰሉት ) ፣ የባህር ምግቦች ለምሳሌ አሳ

3. ዚንክ (Zinc) ያላቸው ምግቦች

ቀይ ስጋ ፣ አቮካዶ እና በከፍተኛ ሁኔታ ኦይስተር(Oyster) የተባለ የባህር ምግብ ላይ ይገኛል። ይሄ ዚንክ ደግሞ በከፍተኛ ቴስቴስትሮን የተባለውን ሆርሞን እና የስፐርም ቁጥርን ይጨምራል።

3. አቮካዶ

በውስጡ ዚንክ፣ ማግኒዝየም እና ጤናማ ቅባት በመያዙ ቴስቴስትሮን የተባለውን ሆርሞን ይጨምራል

4. ማካ ዳቄት

5. ቫይታሚን ዲ

ቫይታሚን ዲ (vitamin D) ያላቸው ምግቦች ከእንቁላል ፣ ወተት እና ከባህር ምግቦች ሲገኙ ቫይታሚን ዲ ደግሞ መውስድ ያለብን በልኩ ከ40 እስከ 100 ናኖሞል በሊተር ነው። ይሄም ቴስቴስትሮን የተባለውን ሆርሞን ይጨምራል::

6. ኦሜጋ 3 ፋትይ አሲድ (Omega-3 fatty acid ) ወይም የአሳ ዘይት (fish oil)

ለምሳሌ፦ አሳ ፣ ሳርዲን እንዲሁም በመድሀኒት ሚዋጥ መልኩም ይገኛሉ። እነዚህ ደግሞ የደም ስር እና የልብን ጤና በመጠበቅ የግንኙነት ችሎታን ያሻሽላሉ።በተጨማሪም ስትሮበሪ፣ ተልባ ፣ የዱባ ፍሬ፧ ሰሊጥ ፣ አረንጓዴ ተክሎች መመገብ ይጠቅማሉ።

7. አጋዥ ንጥረ ነገሮች food supplements

ከተጠቀሱት ምግቦች በተጨማሪ በጥንቃቄ አጋዥ ንጥረ ነገሮች መወሰድ አለባቸው ለምሳሌ:- አሸዋጋንዳ፣ ጂን ሶሚን እና የመሳሰሉት

የማይመከሩ ምግቦች ወይም የማይጠቅሙ ምግቦች

1. ስኳር ያላቸውን ምግቦች እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች

እነዚህን በብዛት ስንመገብ ኢንሱልን የተባለውን ሆርሞን እንዳይሰራ ያደርጋል። ይሄ ኢንሱሊን መጠን መዋዠቅ ደግሞ በሂደት የቴስቴስትሮን እጥረት እንዲመጣ ያደርጋል።

2. ጨው የበዛበት ምግብ መመገብ

ይሄ ደግሞ የደም ግፊት እንዲጨምር በማድረጉ በደም ስር የሚገኙ ግድግዳዎች እንዲጐዳ በማድረጉ ወደ ብልት የሚሄደውን የደም ፍሰት እንዲቀንስ ያደርጋል። ይሄም ስንፈተ ወሲብን ያመጣል።

3. ጮማ ያላቸው ምግቦች

እነዚህ ሰውነታችን ላይ የኮሌስትሮል መጠን ከፍ እንዲል እና ወንዶች ላይ ደግሞ ቴስቴስትሮን የተባለውን ሆርሞንን ወደ ሴት ኢስትሮጅን ወደተባለው ሆርሞን ይቀይረዋል። ይሄ ደግሞ ስንፈተ ወሲብን ያመጣል። ሌላው ቦርጭ በማስከተሉ በራሳቸው አቋም እንዳይተማመኑ እና ግንኙነት ብቃት ላይ ያስቸግራቸዋል ።

4. አልኮል እና ቡና

በብዛት አልኮል መጠቀም በጉበት ላይ ጫና ስለሚያደርስ ቴስቴስትሮን ይቀንሳል::

ቡናም ከመጠን በላይ በብዛት ማለትም በቀን ከ 400 ሚሊ ግራም በላይ መጠቀም የለብንም ምክንያቱም የመድከም ስሜት ያመጣል ስለዚህም የግንኙነት አቅምን ይቀንሳል።

ከምግብም በተጨማሪ ግን ዋናዎቹ የተመጣጠነ ምግብ፣ በቂ እንቅልፍ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ ጭንቀትን መቀነስ እና ጤናማ ግንኙነት ከአጋር ጋር ሲኖር የወሲብ ፍላጐት ይጨምራል።

ምንጭ:- ዶ/ር ሸምስ ዩቱብ ቻናል

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው