የወንድ ልጅ ብልት በየእድሜው መድረስ ያለበት የቁመትና የውፍረት ደረጃዎች

የወንድ ልጅ ብልት በየእድሜው መድረስ ያለበት የቁመትና

የውፍረት ደረጃዎች

ስለወንድ ብልት መጠን በየእድሜው መድረስ ያለበት የቁመትና የውፍረት ደረጃ እንዲሁም በስተጀርባ ያለውን ሳይንስ ምንድነው?

በተለያዩ የዕድሜ ክልል ማለትም ከ አስራ ስምንት እስከ ሰባ ዕድሜ ምን ያህል መሆን አለበት?

ትክክለኛው ቁመት እና ውፍረት አለው የሚባለው ምን ያህል ሲሆን ነው?

የወንድ ብልት መጠንን ለመጨመር የሚያስችሉ ነገሮችን ምንድን ናቸው?

መጀመሪያ የወንድ ብልት መጠን በግለሰቦች መካከል በእጅጉ ሊለያይ እንደሚችል ልብ ማለት አስፈላጊ ነው ቢሆንም ግን አንዳንድ ጥናቶች በየእድሜ ደረጃው ሊሆን የሚገባውን ያሳየናል። ብዙውን ጊዜ በጣም የማወቅ ጉጉት ካላቸው የእድሜ ክልል ስንጀምር.

18 እስከ 20 ዎቹ ዕድሜ

ከ18 እስከ 20 ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች በብዛት ጥያቄውን የሚያነሱት ወጣቶች ማለት ናቸው። journal of sex medicine በተባለው መፅሄት ላይ የወጣው ጥናት እንደሚያመለክተው በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ብልቶቻቸው ቀጥ በሚልበት ጊዜ የብልት ርዝማኔ በአማካይ ከ13.12 cm ሲሆን ዙሪያው ደግሞ 11.66 ሴንቲ ሜትር ገደማ ነው:: እነዚህ መለኪያዎች እንደዘር እና የሰውነት ዓይነት በመሳሰሉት ምክንያቶች ሊለያዩ ይችላሉ ነገር ግን አጠቃላይ መመሪያ ይሰጡናል ማለት ነው። በነዚህ ዓመታት ውስጥ የወንድ ብልት መጠን ማደጉ ሊቀጥል እንደሚችል ልብ ማለት ያስፈልጋል ስለዚህ በነዚህ ልኬት መጠን ባትሆኑ እንኳን መጨነቅ አያስፈልግም።

30ዎቹ ና 40ዎቹ ዕድሜ ክልል

ወንዶች በ30ዎቹ ና 40ዎቹ ዕድሜ ክልል ሲገቡ ብልቶቻቸው መጠን ላይ አንዳንድ ስውር ለውጦች ሊኖሩ እንደሚችል ጥናቶች አመላክተዋል:: British journal of Urology international በተባለው መፅሄት ላይ የወጣ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ማለትም ከ30 እስከ 40 ዎቹ የሚገኙ ወንዶች ብልቶቻቸው ቀጥ በሚልበት ሰዓት ርዝመቱ በአማካይ 12.73 ሴንቲ ሜትር እስከ 14.38 ሴንቲ ሜትር ገደማ እንደሆነ ጥናቱ ያመላክታል።

ይህ መጠነኛ የቁመት መቀነስ ብዙ ጊዜ በቴስቴስትሮን መጠን መቀነስ እና በደም ዝውውር ላይ በሚከሰተው ለውጥ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል። ወንዶች ዕድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ ያው የቴስቴስትሮን መጠንናቸዉ እንደሚቀንስ ይታወቃል። ቴስቴስትሮን ማለት በወንድ የዘር ፍሬ የሚመነጭ ሆርሞን ነው። በብዛት ወንዶች ብልታቸው እንዲያድርግ ከሚያደርጉ ሆርሞን አንዱ ነው.ይሁን እንጂ አሁንም እንደየሰው የሚለያይ መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል ማለት ነው ።

50ዎቹና ከዛ በላይ

50ዎቹና ከዛ በላይ ወዳሉት የዕድሜ ክልል ስንሄድ በነዚህ የእድሜ ክልል ላይ በተለያዩ መልኩ የሚያተኩሩ ጥናቶች ባይኖሩም ያሉት ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የወንድ ብልት መጠን ለአብዛኛው ወንዶች በአንጻራዊ ሁኔታ ቁመቱ ሳይጨምር ሳይቀንስ የተረጋጋ ሆኖ ይቀጥላል። ይሁን እንጂ ከልክ በላይ መወፈር እና አንዳንድ የጤና እክሎች በመጠኑም ቢሆን በቁመቱ ላይ ተጽኖ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጥናቶች ያመላክታሉ።

በ50ዎቹ እና 60ዎቹ ወይም ከዛ በላይ ባሉት ሰዎች ብልታቸው መጠን ላይ ለውጦች ካስተዋሉ የጤና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የጤና ችግር በዚህ እድሜ በብዛት ስለሚከሠት ነው። ወንዶች በተለይ እድሜያቸው ሃምሳ በላይ ሲሆን የተለያዩ ህመሞች ማለትም ከልብ፣ ከደም ስር፣ ከኮሌስትሮል፣ ስኳር ፣ ከግፊት ከመሳሰሉት የቋሚ (Chronic illness) ጋር የሚገናኙ በሽታዎች የሚጀምሩበት ስለሆነ ብልት ጤና ላይ ጫና ማምጣታቸው ስለማይቀር እንዲህ አይነት ነገር ካሳሰባቸው የጤና ባለሙያ በማማከር የጤንነት ሁኔታቸውን ማወቅ ተገቢ ነው።

በመጨረሻም የወንድ ብልት መጠን እንደየእድሜ ክልል ይለያያል እናም አንድን መስፈርት ለማሟላት መጨነቅ አያስፈልግም ከዚህ ይልቅ በአጠቃላይ ፆታ ጤንነት እና እርካታ ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው :: እንዲሁም ከsex partner ጋር ወይም ከሩካቤ አጋር ጋር ግልፅ የሆነ የሃሳብ ልውውጥ ማድረግ እና መነጋገር ወሲባዊ ህይወቶትን ደስተኛ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

የወንድ ልጅ ብልት ቁመትና ውፍረት መጨመር ስለሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን እና ዘዴዎች

ከሁሉ በፊት ግን የወንድ ልጅ ቁመት ለመጨመር ዋስትና የሚሰጥ ዘዴ እንደሌለ መረዳት ያስፈልጋል በርካታ መድኃኒቶች የወንድ ብልት መጠንን በአንድ ወር እስከ አራት ሴንቲ ሜትር እንጨምራለን እያሉ በኢንተርኔት ይዛወራሉ ይሄ እውነት እንዳልሆነ መረዳት ይኖርባችኋል።

ነገር ግን አንዳንድ የጤናማ አኗኗር ዘዴዎች መከተል የብልት ጤንነት ለመጠበቅ ቁመቱንም ውፍረቱንም ለመጠበቅ እንደሚረዱ በጥናት የተረጋገጡ አሉ ከእነዚህም መካከል አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ማድረግ፣ ጤናማ የክብደት መጠን መያዝ፣ የብልት exercises አሉ እነሡን ማድረግ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው። ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ ከብዙ እነዚህን መጥቀስ እንችላለን።

በተጨማሪ ለማንኛውም ዓይነት የስነ-ሩካቤ ወይም ሴክሽዋል ሄልዝ ጉዳዮች የባለሙያ ምክር መጠየቅና ማማከር ከፈለጋችሁ አፔክስ ሴክሽዋል ሄልዝ ክሊኒክ በዚህ ዙሪያ የሚሰራ ድርጅት ሲሆን ቀጠሮ በመያዝ ኤክስፐርት ባለሙያ ምክር እና ህክምና ማግኘት ትችላላችሁ።

ምንጭ፦ ዶ/ር ሸምስ ዩቱብ ቻናል

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው