ከ 7 ጥንዶች መካከል በአማካኝ በአንዳቸው ላይ የመካንነት ችግር ይከሰታል ።ከዚህም ውስጥ 50% በሚሆነው የመካንነት ችግር በወንዱ ምክንያት የሚፈጠር ነው ።
ይህም የሚከሰተው በአብዛኛው የወንድ ዘር (sperm) ቁጥር በተለያዩ ምክንያቶች በመቀነስ ፤ ጤናማ ያልሆነ እና ጥራት የሌለው የወንድ ዘር በመመረቱ ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር የሚያስተላልፉ ቱቦዎች በመዘጋታቸው ምክንያት ነው።
ሌላው በወንዱ ምክንያት የሚመጣ የመካንነት ችግር መንስኤ ስንፈተ-ወሲብ ሲሆኑ ይህ ማለት የወንድ ብልት መቆም አለመቻል/ ግንኙነት ማድረግ አለመቻል ወይንም ማህጸንዋ ሳይደርስ መርጨት(premature ejaculation) ነው።
የወንድ ዘር(sperm) ቁጥር እና ጥራትን የሚቀንሱ ነገሮች በዋናነት የሚከተሉት ናቸው።
የዘር ፍሬ ኢንፌክሽን ለምሳሌ በታዳጊዎች ላይ የሚከሠት ጆሮ ደግፍ / mumps የዘር ፍሬንም በማጥቃቱ ምክንያት የሚከሰት መካንነት (mumps Orchitis) ፤
የሆርሞን ችግሮች ምሳሌ የቴስቴስትሮን ሆርሞን ችግር ፤
የአልኮል መጠጥ ፤ ሲጋራ ማጨስ ማሪዋና እና Steroid የተባሉ መድሃኒቶችን በብዛት መጠቀም የስፐርምን ጥራት ይቀንሳል::
የዘር ማስተላለፊያ ቱቦ ( vas deference) እና የዘር ፍሬ(testis)ላይ በሚፈጠሩ አደጋዎች ና ግጭቶች ምክንያት በሚፈጠር ጠባሳ ምክንያት ቱቦው ሊዘጋ ይችላል።
የጉበትና የኩላሊት በሽታዎች፤ ከመጠን ያለፈ ውፍረት የዘርን ጥራት ይቀንሳሉ።
በተፈጥሮ ምክንያት የዘር ፍሬ ሆድ ውስጥ መቅረት (undescended Testis) ።
አስፈላጊ ምርመራዎች
1) sperm Analysis (የወንድ ዘር ምርመራ)
2) የደም ምርመራዎች ለምሳሌ የሆርሞን ፤ የኩላሊት ና ጉበት ምርመራ ፤ የኮሌስትሮል ምርመራ
3) የዘር ፍሬ ዶፕለር አልትራሳውንድ :: ይህም ያስፈለገው የዘር ፍሬ ላይ የሚገኙት የደም ስሮች ማደግ (varicocele) አለመኖሩን ለማረጋገጥ ነው ።
4) የዘር ፍሬ ናሙና (Testicular biopsy) ይህ የመጨረሻ ደረጀ ምርመራ ነው
የመካንነት ችግር በጥንዶች መካከል አስጨናቂና አሳሳቢ ሊሆን ቢችልም የተለያዩ የህክምና አማራጮች ግን አሉት። ከነዚህም መካከል
1) የመድሀኒት ህክምና :- ለፕሮስቴት ኢንፌክሽን ፀረ-ባክቴሪያ ፤ ለሆርሞን መቀነስ ሆርሞን ህክምና (e.g Gonadotropin therapy) ፤ የስፐርምን መጠንና ጥራት የሚጨምሩ ሰፕለመንቶችና ቫይታሚኖች
2) ሰርጀሪ ለምሣሌ የዘር ፍሬ የደም ስሮች ማደግ (varicocele ) በቀላል ሰርጀሪ ሊስተካከል ይችላል።
3) የመጨረሻው ህክምና በአርቴሽያል መንገድ የወንድ ዘርን በመውሰድ ከሴቷ እንቁላል ጋር ማገናኘት (artificial insemination , IVF ) ነው።
በመጨረሻም በወንድ ልጅ ምክንያት የሚመጣው የመካንነት ችግር በርካታ መንስኤዎች እና በርካታ የህክምና አማራጮች ስላሉት ተገቢውን ምርመራና ህክምና ለማግኘት ሀኪም ጋር ቀርቦ መታየት ያስፈልጋል።
በአካል የባለሙያ(expert) ህክምና ለማግኘት ወደ Apex sexual Health clinic ደውለው ቀጠሮ ይያዙ። 0948339660