ከድንግልና ጋር የተገናኙ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች እና እውነታው 

ሁሉም ድንግል ሴቶች ላይደሙ ይችላሉ ይህም ከአጠቃላይ ድንግል ከሆኑ ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ጾታዊ ግንኙነት ሲያደርጉ 57 በመቶ የሚሆኑት ደም አይፈሳቸውም። 

ሁሉም ድንግል ሴቶች ህመም ላይሰማቸው ይችላሉ ከዚህም ጋር በተገናኘ አንዳንድ ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ጾታዊ ግንኙነት ሲያደርጉ ምንም አይነት ህመም ላይሰማቸው ይችላሉ።

ድንግልና ተመልሶ ይመጣል የሚባል የሳሳተ አስተሳሳተ አለ ነገርግን ድንግልና አንድ ጊዜ ከተወሰደ በኃላ ተመልሶ አይመጣም 

ድንግልና ድፍን ነው ተብሎ ይታሰባል ነገርግን አንዲት ድንግል የሆነች ሴት ለወር አበባ ማሳለፊያ የሚሆን ቀዳዳ ይኖራታል

ከአጠቃላይ ሴቶች 0.03 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ያለ ድንግልና ሊወለዱ ይችላሉእንዲሁም አንዲት ድንግል የሆነች ሴት ለምርመራ በምትሄድበት ወቅት ድንግል መሆንዋን ለዶክተርዋ መናገር ይኖርባታል ይህም በዶክተር ምርመራ ወቅት ድንግልናዋ እንዳይጠፋ ያግዛታል።

ስለዚህ የድንግልና መኖር አለመኖሩን #ከህመም ወይም ከመድማት ጋር መተሳሰር አይችልም 

በሃኪም ምርመራ አንዲት ሴት ድንግል መሆንዋን መቶ ከመቶ ማረጋገጥ አይቻልም

ለዚህም አንዲቲ ሴት ድንግል መሆንዋን መቶ ከመቶ ማረጋገጥ የሚቻለው በጥንዶች መካክል በሚደረግ ግልጽ በሆን ውይይት እና እሷን በማመን ብቻ ነው።

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው