📌ወሲብ አልባ ትዳር/sexless marriage ምንድነው ?
የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ወሲብ አልባ ትዳር የሚባለው በአመት ከ 10 ጊዜ ያነሰ ወሲብ በባለትዳሮች መካከል የሚፈጸም ሲሆን ነው።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወሲብ አልባ ትዳር ከስድስት ባለትዳሮች በአንዳቸው ላይ ይከሰታል ።
መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
1) ያልተመጣጠነ የወሲብ ፍላጎት (mismatched Libido) :- ለምሣሌ የባል ፍላጎት ከፍ ብሎ የሚስት ዝቅ ያለ መሆን ወይንም ፍላጎት ማጣት
2) ውጥረት (Stress) ይህም በተለያየ ምክንያት ይችላል :: ለምሳሌ በስራ፤ በጤና፤ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል።
3) ማህበራዊ ሚዲያን (social Media) በብዛት መጠቀም – በማህበራዊ ሚድያ መጠመድ በባለትዳሮች መካከል ወሲብ እንደይኖር ሊያርግ ይችላል።
4) በግልፅ አለመነጋገር :: ጥንዶች ስለ ወሲብ ፍላጎታቸው ፤ ምንያህል ጊዜ ማድረግ እንዳለባቸው ና ስለ መሳሰሉት ጉዳዮች በግልፅ አለማውራት።
5) በወሲብ አለመጣጣም ፦ የአንደኛው ቀድሞ መጨረስ ወይም አለመርካት በሁለቱም ጥንዶች መካከል አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል :: ለምሳሌ ባል ማላረካት ከሆነ በማለት ሊታቀብ ይችላል።
ይህንን ችግር እንዴት መጠገን ይቻላል?
1) በግልፅ መነጋገር ፦ ከወቀሳና ችግሩ የሌላኛው እንደሆነ ከመናገር ይልቅ የምንፈልገውንና አጋሩ እንድትሆን / እንዲሆን የሚፈልገውን በግልፅ ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው።
2) የግኑኝነት ፕሮግራም ማዘጋጀት ፦ በወር ፤ በሳምንት ስንት ጊዜ መሆን እንዳለበት ተነጋግሮ ፕሮግራም ማዘጋጀት ።
3) የሀኪም እርዳታ መፈለግ ። የፍላጎት ማጣት ወይም አለመጣጣም አንድአንድ ጊዜ በሆርሞን ወይም በሌላ የጤና ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል። የራስመተማመን አለመኖር፤ የጤና ችግር እና ጭንቀት በሀኪም እርዳታ ሊታከም ይችላል።