ከወሲብ ጋር በተገናኘ በርካታ ችግሮች በሴቶች ላይ ይከሰታሉ።ከነዚህም መካከል በዋናነት ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት መኖር አንዱ ነው ።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት 44% የሚሆኑት ሴቶች ከወሲብ ጋር በተገናኘ የተለያዩ ችግሮች ሲኖሩባቸው 38% የሚሆኑት ደግሞ ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት የመኖር ችግር አለባቸው።
አንዲት ሴት ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት ችግር አለባት የሚባለው ያለምንም በቂ ምክንያት (ለምሳሌ በግንኙነት ጊዜ የሚኖር ህመም) ለስድስት ወር እና ከዛ በላይ ለቆየ ጊዜ በጣም ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት ወይም ምንም ዓይነት የወሲብ ፍላጎት ሳይኖራት ሲቀር ነው ።
ይህም ችግር በሴቷ ላይ ድባቴ ፤በራስ መተማመን አለመኖር ፤ ፀፀት ፤ጭንቀት እንዲሁም የግንኙነት መሻከር ሊያስከትልባት ይችላል ።
ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት መኖር የተለያዩ መንስኤዎች ሊኖሩት ይችላል ።
1) የሆርሞን መዛባት
የኤስትሮጅን ፤ ፕሮጄስትሮን ፤ ቴስቴስትሮን እንዲሁም ሌሎች ለጤናማ ወሲብ ፍላጎት መኖር አስፈላጊ የሆኑ ሆርሞኖች ማነስ :: እነዚህ ሆርሞኖች በጭንቀት ፣ ድብርት ፣ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎችን በመውሰድ ፣ በማረጥ እንዲሁም በ አራስነት ጊዜ ሊቀንሱ ይችላሉ ።
2) የስራ መብዛት እና ውጥረት /fatigue and stress
ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ወይም የስራ ብዛት ሴት ልጅን ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንዳይኖራት ሊያደርግ ይችላል ወይም ደግሞ ወሲብ ማድረግ ብትፈልግ እንኳ ለመነቃቃት(arousal) እና የወሲብ ስሜት(mood) ውስጥ ለመግባት ከባድ ሊሆንባት ይችላል።
3) በአጋርዋ ደስተኛ ካልሆነች/ relationship issues
በጥንዶች መካከል ጭቅጭቅ እንዲሁም አለመስማማት ወይም ጥላቻ ካለ ወሲብ የማድረግ ሞራል አይኖራቸውም ። ምንም እንኳን ወንዱ ቢፈልግ እንኳ ሴቲቷ ፍላጎት አይኖራትም ወይም የሴቷ ሰውነት በበቂ ሁኔታ ዝግጁ አይሆንም ።
4) መድሃኒቶች
የተለያዩ በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች የወሲብ ፍላጎትን ሊቀንሱ ይችላሉ ። ለምሳሌ የድብርት መድሃኒቶች ፤ የእርግዝና መከላከያ ታብሌት የወሲብ ፍላጎትን ሊቀንሱ ይችላሉ
5) ጤናማ ያልሆነ የኑሮ ሁኔታ/poor lifestyle
ሲጋራ ማጨስ ፤. አልኮል መጠጣት ፤ ሌሎች ዕፆችን መጠቀም ፤ ያልተመጣጠን ምግብ እንዲሁም ውፍረት የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ያመጣሉ
የመፍትሔ አማራጮች
1) ችግሩ በመድሃኒት ምክንያት የመጣ ከሆነ የሚወስዱትን መድሃኒት ማቆም / መቀየር
ለምሳሌ የእርግዝና መከላከያ ክኒን እየወሰዱ ከሆነ ወደ መርፌ ወይም አይዩዲ(IUD) መቀየር ።
2) የስነ ልቦና ህክምና (psychotherapy)
በተለይ ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት የመኖሩ ምክንያት በተበላሸ ትዳር ግኑኝነት ምክንያት ፤ ጭንቀት ፣ ድብርት የመሳሰሉት ከሆነ በንግግር ህክምና በስነ-ልቦና ባለሙያዎች ( psychotherapist ) ወይም ስነሩካቤ ባለሙያ sex therapist መታከም ይኖርበታል ።
3) የሆርሞን ህክምና
ቴስቴስትሮን በአነስተኛ መጠን ለሴቶችም ሊታዘዝ ይችላል ። ነገር ግን ለሴቶች የሚዘዘው ለወንዶች ከሚታዘዘው 1/10 ብቻ መሆን አለበት ።
4) የመድሃኒት ህክምና
ጭንቅላት ላይ ሚሰሩ የሴቶችን የወሲብ ፍላጎትን የሚጨምሩ እንዲሁም የአሜሪካው መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ያፀደቃቸው ሁለት መድሃኒቶች አሉ ። እነዚህ መድሃኒቶች MSAA(Multi functional serotonin agonist and antagonist ) የሚባለው ምድብ ሲሆኑ፣ እነዚህም
a) Flibancerin
B) Bremelanotide ይባላሉ ።
በአካል የባለሙያ(expert) ህክምና ለማግኘት በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነው Apex medical & sexual Health clinic ደውለው ቀጠሮ ይያዙ።