የታይሮይድ ሆርሞን  መዛባት  መካን ያደርጋል?

በተፈጥሮ ታይሮይድ የተባለ የፊተኛው አንገታችን አካባቢ ያለ ሆርሞን አመንጪ ዕጢ ነው ።

የዚህ ሆርሞን መብዛት ወይም ማነስ (በወንድም ወይም በሴት ላይ ሊሆን ይችላል) ለመካንነት ችግር መንስኤ ሊሆን ይችላል ።

የታይሮይድ ሆርሞን ችግር ሴቶች ላይ የመካንነት ችግር የሚያመጣው የእንቁላል መለቀቅን እንዲሁም የወር አበባ ዑደትን ስለሚያዛባ ነው ።

በወንዶች ላይ ደግሞ የመካንነት ችግር የሚያመጣው የስፐርም ወይም የወንድ ዘር ፈሳሽን ጥራትና ብዛትን ስለሚቀንስ ነው ።

ስለዚህ ልጅ ለመውለድ ተቸግረው ከሆነ ምናልባት የዚህ ሆርሞን ችግር ሊኖርቦት ስለሚችል የታይሮይድ ሆርሞን መጠንዎትን በላቦራቶሪ ምርመራ ማወቅ ያስፈልጋል።

ለመካንነት ችግሩ መንስኤ የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ወይም ማነስ መሆኑ ከተረጋገጠ አስፈላጊውን የ ሆርሞን ማስተካከያ ህክምና በማግኘት ብቻ የመካንነትን ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ማለት ነው ።

የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው :-

በቂ ምግብ እየተመገቡ  ክብደት መቀነስ ፣ ልብ በፍጥነት ሲመታ መሰማት (palpitations ) ፤ መነጫነጭ (የ ሙድ መዛባት) ፣ 

ድካም ፣ የወር አበባ መዛባት ፣የዕጅ መንቀጥቀጥ እና ማላብ የመሳሰሉት ናቸው ።

የታይሮይድ ሆርሞን መቀነስ ምልክቶች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው :-

ክብደት መጨመር ፣ ድካም ፣

ቅዝቃዜን አለመቻል (cold intolerance)  ድባቴ እና የመሳሰሉት ናቸው : :

የሆርሞን መብዛት ወይስ ማነስ መኖሩ ከተረጋገጠ የሆርሞን መጠኑን የሚያስተካክሉ ውጤታማ የሆኑ መድሀኒቶች ስላሉ በቀላሉ ያለምንም ተጨማሪ ህክምና ማርገዝ ይቻላል።

ልብ ይበሉ የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት ችግር ኖሮ እንቅርት (አንገት ላይ እባጭ) ላይኖር ይችላል ። በእርግጠኝነት የታይሮይድ ሆርሞን ችግር መኖሩ የሚታወቀው በላቦራቶሪ የደም ምርመራ ብቻ ነው ።

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው