የወንዶች ግርዛት ጥቅሞች እና የተሳሳቱ አስተሳሰቦች

የወንድ ልጅ #ግርዛት ማለት በወንድ #ብልት አከባቢ ያለ ትርፍ ቆዳን የማስወገድ ሂደት ነው።

በዚህም ሂደት ውስጥ በአለማችን ካሉት ከሶስቱ ወንዶች አንድ ይገረዛል።

የወንድ ልጅ ግርዛት የተለያየ ጥቅሞች አሉት። ከእነዚህም ውስጥ

ኤች_አይቪ_ኤድስ እና የተለያዮ የአባላዘር በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል

የብልት ጫፍ #ኢንፌክሽን ለመከላከል ይረዳል

እንዲሁም ለሴቶች የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል ያግዛል

ከወንድ ልጅ ግርዛት ጋር በተገናኘ የተለያዮ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ይንፀባረቃሉ። ከነዚህም ውስጥ:-

ያልተገረዙ ወንዶች #ስንፈተ #ወሲብ አለባቸው ወይም በግንኙነት ወቅት ቶሎ መጨረስ ይኖርባቸዋል ብሎ ማሰብ ነው።ነገርግን የትኛውም ሳይንሳዊ ጥናት አለመገረዝ ለስንፈተ ወሲብ ወይም ቶሎ መጨረስ ምክንያት እንደሆን አይገልጽም።

ሌላኛው ያልተገረዘ ወንድ #መካን ነው የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ አለ። እስካሁን ከወንድ ልጅ #መካንነት ጋር በተያያዘ በተደረገ ጥናት አለመገረዝ ለመካንነት መንስኤ እንደሆነ አልተጠቀሰም።

በመጨረሻም የተገረዘ ወንድ ሰሜቱ ይቀንሳል የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ አለ። ይህም የወንድ ልጅ ግርዛት እና ስሜቱ ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም።

ስለዚህ የወንድ ልጅ ግርዛት የተለያዮ ጥቅሞች አሉት ነገርግን ከመካንነት እና ከስንፈተ ወሲብ ጋር ግንኙነት የለውም።

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው