ፖርኖግራፊ በወጣቶች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እና እንዴት ማቆም ይቻላል?

ከኢንተርኔት መምጣት ጋር ተያይዞ እድሜያቸው ከ35 አመት በታች የሆኑ ወጣቶች ለተለያዩ አይነት ስንፈተ ወሲብ ተጋላጭ እየሆኑ መጥተዋል። 

ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ ፖርኖግራፊ አዘውትሮ መመልከት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ አንደኛው ግለወሲብ ነው

ግለወሲብ ብዙ ወጣት ወንዶች የሚያስቸግር ልምድ ነው። ይህም ልምድ በማህበራዊ ፣ ሳይኮሎጂያዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል።

በዋነኘት ፖርኖግራፊ የተለያዩ አይነት ችግሮችን በወጣቶች ላይ ያስከትላል ከነዚህም ውስጥ፡

የብልት አለመቆም

የዘር ፈሳሽ ያለመውጣት

ቶሎ መጨረስ

እርካታ ያለመኖር 

ፖሮግራፊን ማየት እንዴት ማቆም እንችላለን

የወሲብ ፊልም ወይም #ፖርኖግራፊ  ቪዲዮ፣ፎቶ እና ሌሎችም ወሲብ ቀስቃሽ ነገሮችን ማየት ማቆም 

አዲስ ልምድ ለማጀመር መሞከር ለምሳሌ ስፖርት መስራት፣ መጽሃፍ ማንበብ፣ ሙዚቃ ማዳመጥ ወይም ሌሎች ልምምዶችን መጀመር

በቸኝነትን ማስወገድ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ ወይም ሌሎች ስራዎችን በመስራት ማሳለፍ

ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

የጤና ባለሙያ ማማከር 

ከጾታ አጋር ጋር በግልጽ በመነጋገር ችግሮችን መፍታት ይቻላል 

         

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው